የአገሬ ስልቻ
ንፋስ የወጠረዉ የአገሬ ስልቻ
ጥፋትና ዉድቀት ከንቱ ጉራ ብቻ
…………….………ታሪክን በዛቻ
………………......ሐቅን በፍራቻ
በአንድነት በፍቅር እኛን የሚያንፅን
ተወልዶ አላየንም ከኢትዮጲያ ማህፀን!
ንግስት ኦሮሚያ
……………….….በወርቃማዉ ሜዳ
……………………..ተወልደሽ ከኦዳ
ዉለሽ ከባሬንቱ አድረሽ ከቦረና
ተምሳሌት የሆንሽዉ የፍቅር ጎዳና
ለግላጋ ቁመትሽ ጎልቶ ከጭላሎ
ሀሪትሽ ማዓዛሽ ቢያዉደኝ ከወሎ
አጊጠሽ በወርቁ ቆመሽ ከወለጋ
ስንቱ ከነፈልሽ ፍቅርሽን ፍለጋ
የወተትሽ ማዕበል ሲናጥ ከቦረና
ደምቀሽ ታየሽ አሉኝ በጭጋግ ዳመና
የገነት ተምሳሌት ዉቢቷ ኮረዳ
በርሽ ሳይንኳኳ ዘልቀዉ ካንቺ ጓዳ
እሳቱ ሲበርደኝ በረዶዉ ሲሞቀኝ
ዉበትሽን ሳደንቅ ልብሽን ሊነጥቀኝ
ከባቱ ሃይቅ ላይ አበባ ታቅፌ
ፍቅርሽን ፍለጋ ብመጣ ከንፌ
ንግስት ኦሮሚያ ዉቢቷ ኮረዳ
ልቤ ተዘርቶልሽ ብበቅል እንደ ኦዳ
ማንን ትመርጫለሽ ከኔና ከባዳ
…………………….ፍርዱን ለአባገዳ
ጆሮሽ ላይ ተኝተዉ ድምፄ እንዳይሰማ
አዋሽ ዳር ቆሜልሽ ዉሃሽን ስጠማ
ቆቃ ላይ ቆሜልሽ ሲዉጠኝ ጭለማ
Ïማ ላይ ቆሜልሽ እያማረኝ ቡና
ከፍልዎሃ ኖሬ ምነዉ አጣሁኝ ጤና
ህይወት ህልም ሆኖብኝ እያለኝ አጥቼ
ህልሜ በተፈታ ከእንቅልፌ ነቅቼ
ከዶኒ ዳን…የግጥም
ማህደር…
የአንድነት ተምሳሌት
ተጠምተዉ ለአንድነት ጡትን የበጠሱ
በደም አስጠምቀዉ ስንቱን ያስለቀሱ
አማትበዉ መስቀሉን ቤት እያቃጠሉ
ለአንድነት ነዉ አሉን ወሮ በላ ሁሉ
በአጥንት የቆመዉ የአንድነት ምሶሶ
የቅዳሴዉ ዉጤት የደም ተሓድሶ
የሚኒሊክ ፀሎት የህፃናት ለቅሳ
ለፍጥረታት ሁሉ ዝናብ ሚያወርድለት
ያለአንዳች ማዳላት ፀሃይ ሚያወጣለት
በክፋት በቶንኮል ሰዎች ሲናከሱ
በፍታሃዊ ሚዛን ሁሉን መለገሱ
ሁሉን ያዋቀረዉ በሂሳብ በስሌት
ፈጣሪ ብቻ ነዉ የአንድነት ተምሳሌት
ከዶኒ ዳን…የግጥም ማህደር
ደብተራና አፍሪካ
የሶስትሺ ዓመት ታሪክ ቀርተን ከደብተራ
በ ሶስት ቀን ተሰለፍን ከአፍሪካ ጎራ
አፍሪካን ቃኘናት ከእግር እስከ አናቷ
ጠይቀን ተረዳን እናት እና አባቱዋን
በጥቁሮች ሚዛን አፍሪካ ስንለካ
ሆድና ጀርባ ነዉ ደብተራና አፍሪካ
በፈጠራ ታሪክ ማንነቴን ገሎ
ፍሩዱን ይሰጠዋል ያደቀቀዉ ቆሎ
ከዶኒ ዳን…የግጥም ማህደር
ዠግናዉ ነብሰ ገዳይ
የዓምላክ በረከት የጥንዶቹ
ምላሽ
ገና ጨቅላ ሳለ ተብሎ ደምመላሽ
ነብስን እንዲበቀል ቢሰጡት
አደራ
ዠግና ሚባልበት ደርሶ የሱ
ተራ
ገሎ ተሰደደ በስጋት ፉከራ
………ፍረሐት አሳዷአቸዉ
…………………ከኔ ቢሰዳቸው
…………..ክላሹን አጥፍተዉ
………መስቀሉን አብርተዉ
ከአገሬ ገቡ ቆባቸዉን ደፍተዉ
የስዉር ፍተሃቱ ሚስጥሩ ሲፈታ
ታስረዉ ይፈታሉ የኛ መሪ ጌታ
ምዕመናን ፊት ቆመዉ እምነትን ሲያድሱ
እምነትና ክህደት ሲቶኖኳኳሱ
አባት ፈገግ አሉ ምዕመናን ሲያለቅሱ
ከዶኒ ዳን…የግጥም ማህደር…