የአንድነት ተምሳሌት
ተጠምተዉ ለአንድነት ጡትን የበጠሱ
በደም አስጠምቀዉ ስንቱን ያስለቀሱ
አማትበዉ መስቀሉን ቤት እያቃጠሉ
ለአንድነት ነዉ አሉን ወሮ በላ ሁሉ
በአጥንት የቆመዉ የአንድነት ምሶሶ
የቅዳሴዉ ዉጤት የደም ተሓድሶ
የሚኒሊክ ፀሎት የህፃናት ለቅሳ
ለፍጥረታት ሁሉ ዝናብ ሚያወርድለት
ያለአንዳች ማዳላት ፀሃይ ሚያወጣለት
በክፋት በቶንኮል ሰዎች ሲናከሱ
በፍታሃዊ ሚዛን ሁሉን መለገሱ
ሁሉን ያዋቀረዉ በሂሳብ በስሌት
ፈጣሪ ብቻ ነዉ የአንድነት ተምሳሌት
ከዶኒ ዳን…የግጥም ማህደር
No comments:
Post a Comment