Sunday, 14 June 2015

ቆይ ማነዉ ዳግማዊ?



ቆይ ማነዉ ዳግማዊ?

ከራሱ ተጣልቶ ከበዓድ ተዋዶ
አንድነት ነው አለኝ ስንቱን አገር ንዶ
የአገር አናት ቆርጦ ለባዳ ቸርችሮ
ቃልኪዳኑን በልቶ በሞት ተደራድሮ
ከኣለቱ ተነስቶ ዉሃ ላይ ነገሰ
አንድነት ነዉ አለኝ ደም እያፈሰሰ
አፍሪካ በበዓድ በነጭ ስትታመስ
አገሬ በገልቱ ስትተረማመስ
አየሁት ወዳጄን ወዳጁን ሲቀላ
ብሎ ሲሰይመዉ ወላሞና ጋላ
ታሪክን ጠቁሙኝ ከአፍሪካ መንደር
ከአጥቢዋ እናት ጡትን ለመዘልዘል
……………………………….ጎራዴ ሚበደር
ቆይ ማነዉ ዳግማዊ………....….?
በቁዱስ መፀሀፉ ስሙ የተከተበ
…………………………..በልቶ የተራበ
………………..…………ዉሃን ያነደደ
…………………..……….ገንብቶ የናደ
……………………….የስዉር ፈጣጣ
………………...…..ከአለቱ የጠጣ
……………..…….ሳይሰበር ማግዶ
………………….….ሳይዘራ አጭዶ
…………….ቆይ ማነው ዳግማዊ
………….…….ሴይጣን ሰላማዊ
………………….….እጅን የቆረጠ
…………………...ጡትን የነጠቀ
……………….…….በደም የከበረ
………………..…….አገር ያከሰረ
ቆይ ማነዉ ዳግማዊ………?
የደምና የአጥንት የሬሳ ሱሰኛ
የትንቢተ ሴይጣን ጡቁር መላአክተኛ
የአንድነት ቅዠቱ ሲፈታልን ህልሙ
ምሶሶሽ ከአጥንት ግድግዳሽ  ከደሙ
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነዉ ቀለሙ

ከዶኒ ዳን…የግጥም ማህደር…

No comments:

Post a Comment