Sunday, 14 June 2015

ንግስት ኦሮሚያ



ግስትሮሚያ

……………….….በወርቃማዉ ሜዳ
 ……………………..ተወልደሽ ከኦዳ
ዉለሽ ከባሬንቱ አድረሽ ከቦረና
ተምሳሌት የሆንሽዉ የፍቅር ጎዳና
ለግላጋ ቁመትሽ ጎልቶ ከጭላሎ
ሀሪትሽ ማዓዛሽ ቢያዉደኝ ከወሎ
አጊጠሽ በወርቁ ቆመሽ ከወለጋ
ስንቱ ከነፈልሽ ፍቅርሽን ፍለጋ
የወተትሽ ማዕበል ሲናጥ ከቦረና
ደምቀሽ ታየሽ አሉኝ በጭጋግ ዳመና
የገነት ተምሳሌት ዉቢቷ ኮረዳ
በርሽ ሳይንኳኳ ዘልቀዉ ካንቺ ጓዳ
እሳቱ ሲበርደኝ በረዶዉ ሲሞቀኝ
ዉበትሽን  ሳደንቅ ልብሽን ሊነጥቀኝ
ከባቱ ሃይቅ ላይ አበባ ታቅፌ
ፍቅርሽን ፍለጋ ብመጣ ከንፌ
ንግስት ኦሮሚያ ዉቢቷ ኮረዳ
ልቤ ተዘርቶልሽ ብበቅል እንደ ኦዳ
ማንን ትመርጫለሽ ከኔና ከባዳ
…………………….ፍርዱን ለአባገዳ
ጆሮሽ ላይ ተኝተዉ ድም እንዳይሰማ
አዋሽ ዳር ቆሜልሽ ዉሃሽን ስጠማ
ቆቃ ላይ ቆሜልሽ ሲዉጠኝ ጭለማ
Ïማ ላይ ቆሜልሽ እያማረኝ  ቡና
ከፍልዎሃ ኖሬ ምነዉ አጣሁኝ ጤና
ህይወት ህልም ሆኖብኝ እያለኝ አጥቼ
ህልሜ በተፈታ ከእንቅልፌ ነቅቼ

ከዶኒ ዳን…የግጥም ማህደር…

No comments:

Post a Comment