ቆይ የማነሽ አንቺ?
አዲስ ነሽ ፊንፊኔ
የባዳ…. ነሽ…. የኔ
ቆይ የማነሽ አንቺ
አግብተሸ ስትፈቺ
ምነዉ ሳትሰለቺ
ኦዳዉ ነዉ መስቀሉ
ማን ፈረመዉ ዉሉን
ማነዉ አባ ወራ
ኦሮሞ ነዉ አማራ
ሶማሌ ነዉ ትግሬ
ስልጤ ነዉ አደሬ
ዉበትሽ ድንቅ ነው ዛሬም ሳታረጂ
ስንቱን ስታገቢ ስንቱን ስታፋጂ
ቆመሽ ያለዛቢያ ስትሽከረከሪ
ጨፍልቀሽ በአንድነት ሁሉን ስታኖሪ
የሚዳኝሽ ጠፍቶ ባሎችሽ ቢበዙ
መቋቋም ተሳነሽ የቅናት መዘዙን
(ከዶኒ ዳን…የግጥም
ማህደር…)
No comments:
Post a Comment