አኪራ ታተመ
ተሹመዉ በጡንቻ አገርን ሲመሩ
ሲያነሱ ሲጥሉ ዝተዉ ሲፎኩሩ
ከአናታችን ነግሰዉ
ያለፊደል ደርሰዉ
ሳይጋግሩ ጎርሰዉ
በጠባቂ ታጥረዉ
ተጠርጣሪን አስረዉ
ከሞት ሲሸሸጉ
ምነዉ ተገደዱ
ጊዜ የማይመርጠዉ ቀን ይሁን ጨለማ
ቅርፁ የማይታየዉ ድምጡ የማይሰማዉ
ዘልቆ ገባ አሉኝ ከቤተ መንግስቱ
እኔንስ ገረመኝ አለማንኳኳቱ
በሞት ተሸንፈዉ በፍተሐዊ ምርጫ
ሊቀርቡ ነዉ አሉኝ ሰማይ ቤት ፍጥጫ
ተቃዋሚ ሳይኖር ምነዉ አጡ ማምለጫ
ተብትበዉ ጠምጥመዉ አገሬን ሲገዙ
ከተግባርም ርቀዉ በህልሞትም ሲያዙ
ምን አሉ በሞቴ ተገደዉ ሲጓዋዙ
አልተከራከሩም
ጋርዶች አልነበሩም
ቆይ ምንድነዉ ጉዱ
እንዲሁ ሲገደዱ
ነብሶ ስትነጠቅ ስዉር ሲዳበሱ
በሽጉጥ አናቱን ምነዉ ሳያፈርሱ
በፀረ-ሽብሩ ህግ ለምንስ ሳይከሱት
አኛን ተሳናብተዉ መቃብር ሲወርዱ
በሰላም ደርሰዋል እንዴት ነዉ መንገዱ
ማነዉ የተቀበሎት አበባ ታቅፎ
በሱፍ ሽክ ብሎ በወግ ተሰልፎ
ምን አዩ በሞቴ በድቅድቅ ጭለማ
ምሽት እንዴት ነበር የቀብር ዋዜማ
ከማያዉቁት አገር ከሄዱበት መንደር
ሲገለጥ መፀሀፉ የእዉነት ማህደር
ምላስም ታሰረ
ጉልበት ተሰበረ
ብልጠትም ከሰረ
ክብሮትም ወደቀ
ማንነት ደቀቀ
ሁሉም አከተመ…
የደረሱት መፀሀፍ
… አኪራ ታተመ