ዓለም እንዴት ትሁን?
ፈጣሪ ቢወድሽ ከካዝናዉ የሸለመሽ
ቅናት ምቀኝነት በቀን ያጨለመሽ
ከገበታሽ ጠግቦ ጥጋብን ያገሳ
አንዱ ሲያዜምልሽ ሌላኛዉ ወቀሳ
ጠላትሽ ቢሠላ ስንት ነዉ ብዛቱ?
ይዘቱን ታዉቂያለሽ ስንት ነዉ ክብደቱ?
ወዳጅሽ ስንት ነዉ ላንቺ የተጨነቀ
ሳይወድ በግዱ አገር የለቀቀ
ከሞት ከእስራት ድንገት ያመለጠ
ባንቺ ናፍቆት ግሎ በአዉሮፓ አገር በረዶ ያቀለጠ
ስንቱ ነዉ ዘራፊሽ…………?
ኦዳን ተገን አርጎ ፎቅ የደረደረ
ማንነቱን ሽጦ ሆዱን ያከበረ
እዉነትን ተዉሶሽ ቅጥፈት ያበደረሽ
በጠላት ቀስተኛ እናት
ስትመታ
ጋሻ የሚሆነዉ ልጅ
ነበር መከታ
ያለው ከተራበ የሌዉ ምን ይሁን?
በደል ፅድቅ ከሆነ ዓለም እንዴት ትሁን?
donidan_2016
No comments:
Post a Comment