Saturday, 25 August 2018

ያሳጣቸው ጤና

     #ያሳጣቸው #ጤና!!
በቦረና ኦሮሞ በአርብቶአደሩ
እምነት ብቻ ካሎት ዶላር ይዘርዝሩ
ቦረና ሰው ያምናል ልክ እንደፈጣሪ
ሰንጋውን ያስጭናል አሰልፎ ጋሪ
ሰንጋውን አስጭኖ ገንዘብን ፍለጋ
እምነቱ ይበላል ሌሊቱ ሳይነጋ
በፈጣሪ ምሎ ለዕውነት ቃሉን ሰቶ
ሆዱን ይቆዝራል የሰው ሃቅ በለቶ
በክረምት በበጋ የለፋው ልፋቱ
አንጀት ያሳርራል ሲሆንበት ከንቱ
የቦረናን ዋቃ የሁላችን ጌታን
እንለምነዋለን..................
የሰው ሃቅ የበላን እንዲያሳጣው ፋታ
ሰላም እንዳያገኝ በላ እንዲወርድበት
ሐዘን ከመከራ ችግር እንዲያድርበት
ሰው ሃቅ በልተው..................
የገነቡት ህንፃ የገዙት መኪና
ሰላሙን ይንሳቸው ያሳጣቸው ጤና!!
#AMIN
@Abdulmalik
#ULAGA

No comments:

Post a Comment